Contact Us on Social Media

asxaa oromiyaa

VIA Oromia communication Bureau

ኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ቢሮ ታህሳስ 5 ቀን 2010 ዓ.ም (ከኦሮሚኛ ቃል በቃል የተተሮጎመ ኦሮሚኛውን ከታች ይመልከቱ)
============================================================

በጨለንቆ በተፈፅመው የጅምላ ግድያ በስተጀርባ ማን ነው ያለው ?

የኢፌዲሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 87 (3) ስር የአገር መከላከያ ሰራዊት የአገርን ሉዓላዊነት ለማሰከበር ነው የተቋቋመው። በዚሁ ንዑስ አንቀፅ 4 እና 5 ስር የአገር መከላከያ ሰራዊት በማንኛውኝ ጊዜ ለህገመንገስቱ ታዛዥ በመሆን ለፖለቲካ ፓርቲዎች ውግንና ሳያሳይ ነፃ ሆኖ የአገር ደህንነት የመጠበቅ ስራውን እንደሚሰራ ይደነግጋል።

ይሄው የመከላከያ ሰራዊቱ ከውጭ የሚመጣውን የአገሪቱን ጠላት ለመከላከል በአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች የተገነባ ከተቋቋመለት አላማ ውጭ ታሪካዊ ስህተቶችን በህዘቦች ላይ ሲፈፅም ታይቷል። የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 8 (1-5) ስር የአገሪቱ ህዝቦች ሉዓላዊነት አስመልክቶ የአገሪቱ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦና ህዝቦች የኢተዮጵያ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት መሆናቸው ይደነግጋል።
ይህ ህገ-መንግስት የአገሪቷ የሀጎች ሁሉ የበላይ ሆኖ ባለበት ሁኔታ የስልጣን ባለቤት የአገሪቷ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦና ህዝቦች ሆኖ እያሉ በማንኛው የአገሪቱ ባለስልጣን ውሳኔ ወይንም በማንኛውም የመንግስት አካል ወሳኔ ከህገ-መንግስቱ ጋር የሚጋጭ ተግባር በፈፀም በማይቻልበት ሁኔታ የአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ከተሰጠው የስልጣን ገደብ ጥሶ ህዝቡ ውስጥ በመግባት ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

ለዚህ መልካም ማሳያ የሚሆን ጥቂት ሀላፍነት በጎደላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በሜታ ወረዳ በጨለንቆ ከተማ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የተፈፀመ ዘግናኝ የጅምላ ፍጂት ነው። ከዚህ ጅምላ ፍጂት በስተጀርባ ማነው ያለው የሚለው ጥያቄ ለህዝቡ መመለስ ግዴታ ነው። ከዚህ አፀያፊ ድርጊት በስተጀርባ ያለ ሃይል ሊጋለጥ ይገባል። ለህግም መቅረብ ይኖርበታል።

በአገራችን ህገ-መንግስት መሰረት የመጨረሻው የመከላከያ ሰራዊቱ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስተረሩ ነው። እንደዝህ አይነት ወንጀሎች ሲፈፀሙ ከእውቅናው ውጭ ከሆነ መርምሮ የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ የሚገባው ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህንን ከማድረግ ፋንታ ተመሳሳይ ወንጀሎች በሚፈፀሙበት ውቅት ዝምታን መምረጥ ለሚፈፀመው ወንጀል እውቅና መስጠቱን ያሳያል።

የመከላከያ ሰራዊቱ የኦሮምያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ወደክልሉ እንዲገባ ጥሪ ባላደረገለት ሁኔታ የክልሉን ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤትነት መብት በመግፈፍ የፈፀመውና እየፈፀመ የሚገኘው ወንጀል የአገሪቱን ህገ-መንግስት በግልፅ የጣሰ ነው። ይህንን ስንል የመከላከያ ሰራዊቱ በሙሉ የዚህ ችግር ሰለባናቸው ማለታችን ሳይሆን የህዝቡ ወገንተኝነት ያላቸው የመከላከያ አባላት እንዳሉ ሁሉ ጥቂት የሰራዊቱ አባላት ግን ሆፐን ብለው ህዝቡ ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆናቸው በግልፅ እየታየ ነው።

በመሆኑም የህዝቡን ደህንነትና ሰላም ከማስተጠበቅ ፋንታ የህዝቡን ሰላም እያደፈረሱና ጉዳት እያደረሱ ያሉ የሰራዊቱ አባላት ለህግ ሊቀርቡ ይገባል። የህግ የበላይነት እንዲከበር የሚመለከተው አካላት ሁሉ ካልተንቀሳቀሰ ነገም ተመሳሳይ ችግር መከሰቱ የማይቀር ነው። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም በዚህ ደረጃ ትኩረት ሰጥቶበት የመፍትሄ አቅጣጫ በማሰቀመጥ እየሰራ ይገኛል። የመከላከያ ሰራዊቱ የቆመለትን አላማ በመዘንጋት ያለሙያው በህዝቡ ውስጥ በመግባት ማወክ የማንን አላማ ከግብ ለማድረስ እንደሆነ ተለይቶ መታወቅ አለበት።

የፌዴራል መንግስትና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ይህንን አሰቃቂ ወንጀል የፈፀሙትን የሰራዊቱ አባላትእና ከበስተጀርባ ሆነው ያቀዱትን ለህግ ለማቅረብ እየሰሩ ይገኛሉ። የሚደረስበት ውጤትም ለህዝቡ ይፋ ይደረጋል። የክልሉ የጸጥታ አካላትም የክልሉን ህዝብ ሰላም ለማስከበር ማንኛውንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል ከማንኛውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆን አለባቸው። ህዝቡ አላስፈላጊ መስዋዕትነት እንዳይከፍል በመረጋጋትና በጥንቃቄ ሊንቀሳቀስ ይገባል። ከሁሉም በላይ መደማመጥና በአንድነት መንቀሳቀስ እጅግ ወሳኝ ነው።

የኦሮሞ ህዝብ ላቀረበው የመብት ጥያቄ፣ መብቱን በሰላማዊ ትግል ለማስከበር ስለተንቀሳቀሰ በቄዬው ላይ በጅምላና በተናጠል የመገደል፣ ከሚኖርበት አከባቢ የመፈናቀልና ሽብር ሊፈፀምበት አይገባም። የኦሮሞ ህዝብ ትናንት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር ደሙን የከፈለና አገሪቷ ሉዓላዊነቷን ጥብቃ ለዛሬ እንድትበቃ ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመሆን የተጠየቀውን ዋጋ ሁሉ የከፈለ ህዝብ ነው። የአገሪቷ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ትናንት ያንን ሁሉ መስዋዕትነት የከፈሉት ለዚሁ አገር አንድነት፣ ሰላምና ብልፅግና ነው። ዛሬም ጥቂት የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ህዝቡ የጣለባቸውንሃላፊነት በመዘንጋት ሰላማዊውን ህዝብ በቄዬው ላይ መግደል አስነዋሪ ነው። በመሆኑም ይህንን ወንጀል የፈፀሙትን አካላት ለህግ ማቅረብ ያስፈልጋል። ይህንን ለማድረግ በአንድ ባንድራ ስር አብረን ለምንኖር የአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች አንድነትና ድጋፍ ጊዜው አሁን ነው።

በጨለንቆ በተፈፀመው የጅምላ ግድያ በስተጀርባ ማን ነው ያለው? ለሚለው ጥያዌ ህቡ በግልፅ መልስ ሊያገኝ ይገባል።

Oromia communication Bureau

Add comment


Security code
Refresh