Contact Us on Social Media

Image may contain: one or more people and outdoor

Credit to Addisu arega Kitesa 

ኦሮሚያ የሁሉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቤት ናት። የኦሮሞ ህዝብ በወንድማማችነት እና በአብሮነት መኖር የሚያዉቅ፥ ማቀፍ፥ ማጉረስ ባህሉ የሆነ በችግር እና በመከራ ጊዜያት አብሮ መቆም የሚያዉቅ ታላቅ ህዝብ ነዉ። ባለፈዉ ሳምንት ቡኖ በደሌ ዞን ተፈጥሮ የነበረዉን ችግር ለማረጋጋት ወደ ስፍራዉ ተጉዤ ነበር። በአካባቢዉ ትከስቶ የነበረዉ ችግር ጉዳት እንዳያደርስባቸዉ በመስጋት ገቺ ከተማ ተጠልልዉ የነበሩ ዜጎቻችንን ለማየት ወደ ተጠለሉበት ስፍራ ሄጄ ነበር። በመጠለያዉ ያየሁትን ገጠመኝ ላዉጋችሁ።

በመጠለያዉ ተጠልለዉ ያሉትን በመጎብኘት ላይ እያለን አንድ እጃችዉ ላይ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸዉ ጎልማሳ የተሰበረ እጃቸዉ በቀርከሃ ታስሮ እያቃስቱ መጡ። ሰዉዬዉ ጉዳቱ እንዴት እንደደረሰባቸዉ ጠየቅናቸዉ። ሰዉየዉ አቶ መንግስቱ ፀጋ ይባላሉ። የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ ናችዉ። በግምት የ60 አመት አመት አዛውንት ሲሆኑ በቀበሌያቸው በተነሳው ግርግር በ1977 ዓ.ም በሰፈራ ምክንያት ከትግራይ የመጡ ጎረቤቶቻቸውን ቤት ለማቃጠል ሙከራ ያደረጉ ግለሰቦችን "እኔ እያለሁ እነሱን ለይታችሁ ልታጠቁ አትችሉም፤ ለዘመናት በፍቅር ኖርን እንጅ ምን አጠፉ?'' በማለታቸው እና መከላከል በመጀመራቸው በደረሰባቸው ድብደባ እጃቸው በሁከት ፈጣሪዎች በተፈፀመባቸዉ ጥቃት መሰበሩን እያለቀሱ ነገሩን። የአቶ ፀጋ የፈፀሙት የወንድሞቻቸዉን ቤት የመከላከል ተግባር ትክክለኛ የኦሮሞነት ተግባር ነዉ። ኦሮሞ ጎሮቤቱንና ወንድሙን ከጥቃት ይከላከላል እንጂ፥ ከጥቃት እየተከላከለዉ ቀድሞት ይሞታል እንጂ በወንድም ብሄሮች ላይ ጥቃት አይፈፅምም። ኦሮሚያ ክልል ዉስጥ የሚኖር ተጋሩ ላይ ጥቃት የሚያስብ ማንኛዉም ሰዉ የኦሮሞ ህዝብ ጠላት ነዉ። ኦሮሚያ ክልል ዉስጥ የሚኖር ጉራጌ ላይ ጥቃት የሚያስብ ማንኛዉም ሰዉ የኦሮሞ ህዝብ ጠላት ነዉ። ኦሮሚያ ክልል ዉስጥ የሚኖር አማራ ላይ ጥቃት የሚያስብ ማንኛዉም ሰዉ የኦሮሞ ህዝብ ጠላት ነዉ። ኦሮሚያ ክልል ዉስጥ የሚኖር የማንኛዉም ብሄር ተወላጅ ላይ ጥቃት የሚያስብ ማንኛዉም ሰዉ የኦሮሞ ህዝብ ጠላት ነዉ። በዛሬዉ ዕለት በነቀምቴ ከተማ የተከሰተዉ አስነዋሪ ተግባር የኦሮሞ ህዝብን አይወክልም። እንደዚህ አይነት አስነዋሪ ተግባሮች ደግመዉ እንዳይከሰቱ ጠንክረን እንሰራለን።

በዚህ አጋጣሚ የክልላችን ህዝብ በአንድነት በመቆም የሁከት ፈጣሪዎችን የሁከት እና የብጥብጥ አጀንዳ በማክሸፍ ክልላችን የሰላም፣ የወንድማማችነት እና በአንድነት በአብሮነት የምንኖርባት ክልል እንድትሆን መላዉ የክልላችን ህዝብ ከመንግስት እና ከጸጥታ አስከባሪ አካላት ጎን በመቆም የሁከት እና የብጥብጥ አጀንዳዎችን እንዲታገል ጥሪያችንን እናቀርባለን።

 

 

asxaa oromiyaa

VIA Oromia communication Bureau

ኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ቢሮ ታህሳስ 5 ቀን 2010 ዓ.ም (ከኦሮሚኛ ቃል በቃል የተተሮጎመ ኦሮሚኛውን ከታች ይመልከቱ)
============================================================

በጨለንቆ በተፈፅመው የጅምላ ግድያ በስተጀርባ ማን ነው ያለው ?

የኢፌዲሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 87 (3) ስር የአገር መከላከያ ሰራዊት የአገርን ሉዓላዊነት ለማሰከበር ነው የተቋቋመው። በዚሁ ንዑስ አንቀፅ 4 እና 5 ስር የአገር መከላከያ ሰራዊት በማንኛውኝ ጊዜ ለህገመንገስቱ ታዛዥ በመሆን ለፖለቲካ ፓርቲዎች ውግንና ሳያሳይ ነፃ ሆኖ የአገር ደህንነት የመጠበቅ ስራውን እንደሚሰራ ይደነግጋል።

ይሄው የመከላከያ ሰራዊቱ ከውጭ የሚመጣውን የአገሪቱን ጠላት ለመከላከል በአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች የተገነባ ከተቋቋመለት አላማ ውጭ ታሪካዊ ስህተቶችን በህዘቦች ላይ ሲፈፅም ታይቷል። የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 8 (1-5) ስር የአገሪቱ ህዝቦች ሉዓላዊነት አስመልክቶ የአገሪቱ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦና ህዝቦች የኢተዮጵያ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት መሆናቸው ይደነግጋል።
ይህ ህገ-መንግስት የአገሪቷ የሀጎች ሁሉ የበላይ ሆኖ ባለበት ሁኔታ የስልጣን ባለቤት የአገሪቷ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦና ህዝቦች ሆኖ እያሉ በማንኛው የአገሪቱ ባለስልጣን ውሳኔ ወይንም በማንኛውም የመንግስት አካል ወሳኔ ከህገ-መንግስቱ ጋር የሚጋጭ ተግባር በፈፀም በማይቻልበት ሁኔታ የአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ከተሰጠው የስልጣን ገደብ ጥሶ ህዝቡ ውስጥ በመግባት ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

ለዚህ መልካም ማሳያ የሚሆን ጥቂት ሀላፍነት በጎደላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በሜታ ወረዳ በጨለንቆ ከተማ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የተፈፀመ ዘግናኝ የጅምላ ፍጂት ነው። ከዚህ ጅምላ ፍጂት በስተጀርባ ማነው ያለው የሚለው ጥያቄ ለህዝቡ መመለስ ግዴታ ነው። ከዚህ አፀያፊ ድርጊት በስተጀርባ ያለ ሃይል ሊጋለጥ ይገባል። ለህግም መቅረብ ይኖርበታል።

በአገራችን ህገ-መንግስት መሰረት የመጨረሻው የመከላከያ ሰራዊቱ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስተረሩ ነው። እንደዝህ አይነት ወንጀሎች ሲፈፀሙ ከእውቅናው ውጭ ከሆነ መርምሮ የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ የሚገባው ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህንን ከማድረግ ፋንታ ተመሳሳይ ወንጀሎች በሚፈፀሙበት ውቅት ዝምታን መምረጥ ለሚፈፀመው ወንጀል እውቅና መስጠቱን ያሳያል።

የመከላከያ ሰራዊቱ የኦሮምያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ወደክልሉ እንዲገባ ጥሪ ባላደረገለት ሁኔታ የክልሉን ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤትነት መብት በመግፈፍ የፈፀመውና እየፈፀመ የሚገኘው ወንጀል የአገሪቱን ህገ-መንግስት በግልፅ የጣሰ ነው። ይህንን ስንል የመከላከያ ሰራዊቱ በሙሉ የዚህ ችግር ሰለባናቸው ማለታችን ሳይሆን የህዝቡ ወገንተኝነት ያላቸው የመከላከያ አባላት እንዳሉ ሁሉ ጥቂት የሰራዊቱ አባላት ግን ሆፐን ብለው ህዝቡ ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆናቸው በግልፅ እየታየ ነው።

በመሆኑም የህዝቡን ደህንነትና ሰላም ከማስተጠበቅ ፋንታ የህዝቡን ሰላም እያደፈረሱና ጉዳት እያደረሱ ያሉ የሰራዊቱ አባላት ለህግ ሊቀርቡ ይገባል። የህግ የበላይነት እንዲከበር የሚመለከተው አካላት ሁሉ ካልተንቀሳቀሰ ነገም ተመሳሳይ ችግር መከሰቱ የማይቀር ነው። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም በዚህ ደረጃ ትኩረት ሰጥቶበት የመፍትሄ አቅጣጫ በማሰቀመጥ እየሰራ ይገኛል። የመከላከያ ሰራዊቱ የቆመለትን አላማ በመዘንጋት ያለሙያው በህዝቡ ውስጥ በመግባት ማወክ የማንን አላማ ከግብ ለማድረስ እንደሆነ ተለይቶ መታወቅ አለበት።

የፌዴራል መንግስትና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ይህንን አሰቃቂ ወንጀል የፈፀሙትን የሰራዊቱ አባላትእና ከበስተጀርባ ሆነው ያቀዱትን ለህግ ለማቅረብ እየሰሩ ይገኛሉ። የሚደረስበት ውጤትም ለህዝቡ ይፋ ይደረጋል። የክልሉ የጸጥታ አካላትም የክልሉን ህዝብ ሰላም ለማስከበር ማንኛውንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል ከማንኛውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆን አለባቸው። ህዝቡ አላስፈላጊ መስዋዕትነት እንዳይከፍል በመረጋጋትና በጥንቃቄ ሊንቀሳቀስ ይገባል። ከሁሉም በላይ መደማመጥና በአንድነት መንቀሳቀስ እጅግ ወሳኝ ነው።

የኦሮሞ ህዝብ ላቀረበው የመብት ጥያቄ፣ መብቱን በሰላማዊ ትግል ለማስከበር ስለተንቀሳቀሰ በቄዬው ላይ በጅምላና በተናጠል የመገደል፣ ከሚኖርበት አከባቢ የመፈናቀልና ሽብር ሊፈፀምበት አይገባም። የኦሮሞ ህዝብ ትናንት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር ደሙን የከፈለና አገሪቷ ሉዓላዊነቷን ጥብቃ ለዛሬ እንድትበቃ ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመሆን የተጠየቀውን ዋጋ ሁሉ የከፈለ ህዝብ ነው። የአገሪቷ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ትናንት ያንን ሁሉ መስዋዕትነት የከፈሉት ለዚሁ አገር አንድነት፣ ሰላምና ብልፅግና ነው። ዛሬም ጥቂት የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ህዝቡ የጣለባቸውንሃላፊነት በመዘንጋት ሰላማዊውን ህዝብ በቄዬው ላይ መግደል አስነዋሪ ነው። በመሆኑም ይህንን ወንጀል የፈፀሙትን አካላት ለህግ ማቅረብ ያስፈልጋል። ይህንን ለማድረግ በአንድ ባንድራ ስር አብረን ለምንኖር የአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች አንድነትና ድጋፍ ጊዜው አሁን ነው።

በጨለንቆ በተፈፀመው የጅምላ ግድያ በስተጀርባ ማን ነው ያለው? ለሚለው ጥያዌ ህቡ በግልፅ መልስ ሊያገኝ ይገባል።

Oromia communication Bureau

 Mekele

በመቀሌው የህወሓት መድረክ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የተሸረበው ሴራ ሚስጥሮች ማፈትለክ ጀመሩ (ሶስተኛ ክፍል)
=====================================
የኦሮሞን ሕዝብ ሙሉ ተቃባይነት ያገኘውን የተሃድሶውን አመራር አስወግዶ አዲስ ኦህዴድ የማደራጀት ሽርጉድ ተጋለጠ 
#ኦዳ_ነቤ_ከፍንፍኔ
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦

Credit to Sandaba Boka
የወያኔ ቡድን ባለፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያን ሲገዛ በነበረባቸው ዓመታት አንዴ የመንግስትነት ባህሪይ ሌላ ጊዜ የሽፍትነት ባህሪይውን እየቀያየረ የተለያዩ ታክቲኮችን በመጠቀም እስከ ዛሬ ማንም ትርጉሙን መናገር ባልቻለው “የአንድ ፖለቲካል ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ምስረታ” ሽፋን ህዝቡን እያደናገረ በሌላ በኩል ደግሞ የነገ አለኝታው አድርጎ የመሰረተውን የኪራይ ሰብሳቢ ቡድን አደራጅቶ ወደ ኦሮሚያና ጋምቤላ በማሰማራት በኢቨስትመንት ሲዘርፍና ሲያዘርፍ ለመቆየቱ የአደባባይ ሚስጥር ነው። የሚገርመው ነገር ይህ የዘረፋ አካሄዱ ከረር ብሎ ሲሄድ ከህዝብ ዘንድ የሚሰማውን ሮሮ ለማስቆም የሚጠቀመው “የሙስና ድርጊቱ አደገኛ ደረጃ ላይ የደረሰ ስለሆነ መገምገም አለበት” በሚል አባል ድርጅቶቹን ይገመግምና የሰረቀውን ለመደበቅ እንዲያመቸው “ሁላችንም በድርጊት ባንሳተፍም በአመለካከት ከዚህ ነፃ ስላልሆን ተጠያቂነቱ እኩል ነው” በሚል ግራ የበሚያጋባ ድምዳሜ ይወጣና ለዚሁ ብሎ ባደረጃቸው ሚዲያዎቹ አየሩን ሞልቶ ግራ ማጋባቱን ያጠናክራል።
ይህ አካሄድ በረዘመ ቁጥር የሚጠቀመው ወገን አነስተኛ፤ ነገር ግን ደግሞ በጉልበት እየፈረጠመ መምጣቱ ከህዝብ ጋር እያጋጨው መጣ። ይህ ህዝባዊ ቁጣ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በተለይም በወጣቶች ዘንድ እየተፋፋመ የመጣውን ህዝባዊ አብዮት ለማፈን የተጠቀመበት የሃይል እርምጃ ለጊዜው ችግሩን ያቀዘቀዘ ቢመስልም ህዝባዊ መሰረቱ እየተጠናከረ በመምጣቱ የፌዴራሉን መንግስት ህልውና ለአደጋ ማጋለጡን ሲረዱ ተደርጎ በማይታወቅ ሁኔታ የአህአዴግ ምክር ቤት ተብዬውን ለአስራ አምስት ቀናት ከወቀሩት በሁዋላ የኢህአዴግ የ15 ዓመታት የተሀድሶ ግምገማ መጠናቀቁን በሚዲያ ነግረውን በየአባል ድርጅቶቹ ተመሳሳይ ተሀድሶ ተካህዶ ህዝባዊ አብዮቱን ማፈን ወይም ማለዘብ የሚችል ቡድን ወደ አመራር እንዲመጣ ጥገናዊ ለውጦች እንዲካሄዱ ወጥ መመሪያ ተሰጥቶ ሁሉም ወደየክልልሉ የቤት ስራውን ይዞ ገባ። 
በኦሮሚያ በማህበራዊ ሚዲያ የተመራው የወጣቶች እንቅስቃሴ ህዝባዊ መሰረት እየያዘ መምጣቱ የክልሉ የተሀድሶ እንቅስቃሴ በጥንቃቄ እንዲመራ ተደርጎ ህዝበ አዳም አዳማ ገልማ አባ ገዳ ከተመ። የተካሄደው የተሀድሶ መድረክ ምንም እንኩዋን ጠንከር ያለ ቢመስልም በመጨረሻ የነበረው በሁለቱ የድርጅት መሪዎች መካከል የጥሎ ማለፍ ፍትግያው ድራማ ህዝባዊነታቸውን ትዝብት ውስጥ የጣለ ነበር። በተወሰነለት የጊዜ ገደብ ማለቅ የነበረበት የተሃድሶ መድረክ የህዝብን ብሶት ይዘው በገቡ አባላትና ከበላይ አካል “ወይ ተፈጽማለህ ወይ ያልቅልሀል” ቀጭን መመሪያ ይዘው በመጡ አባላት መካከል የውጥረቱ ትኩሳት እያየለ በምጣቱ መድረኩ በሁለት ቀናት ተራዘመ። ህዝባዊ ጥያቄ ይዞ የቀረበው ወገን አልበገርነቱን አጠናክሮ በመቀጠሉ በኢህአዴግ የአገዛዝ ታሪክ ተደርጎ በማይተወቅ መልኩ ያልተጠበቀው ቡድን ወደ አመራር ብቅ አለ። እርስበርስ ሲጠላለፉ የነበሩ የቀድሞ የድርጅቱ መሪዎችም ተሀድሶውን የመምራት ብቃት የላችሁም ተብለው በትረ መንግስታቸውን አስረከቡ።
ይህ ክስተት ሁለት አንደምታ ይዞ ብቅ ማለቱ አልቀረም፤ ባንድ በኩል ለዓመታት የቆየውን የመልካም አስተዳደር ችግር እና የወጣቱን የስራ አጥነት ችግር ሊፈታ የሚችል አመራር ሊሆን ይችላል የሚል ግምት በሰፊው ህዝብ ዘንድ በአዎንታዊ መልኩ ሲወሰድ፤ ከህወሓት እይታ ውጭ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ያልወደዱና በስጋት ያዩ ወገኖች ደግመው “ይህች ባቄላ ካደረች…” በሚል አስተሳሰብ ከጅምሩ መሰናክሎችን መፍጠር መጀመራቸው አልቀረም። የተሀድሶው ህደት ሳይጣቀቅ ገና በጥዋቱ ከወደ ጂግጂጋ የተተኮሰው ላውንቸር አዲሱ የኦሮሚያ አመራር የኦነግ ስብስብና ፀረ ፌዴራሊዝም እንደሆነና አቶ ለማ መገርሳም በህዝብ ያልተመረጠ መሪ መሆኑን የሚያበስር አንድ ጽሁፍ በአይጋ ፎረም ተለቀቀ። ይህ ለሰሚው ግራ የሆነ ጽሁፍ ለምን የሚል ሀሳብ የሚያስነሳ ቢሆንም ገና በተሀድሶው ወቅት በለማ መገርሳ የሚመራው ቡድን ከአለቆች እቅድ ውጭ ወደ ስልጣን መምጣቱን ለመጠቆምና በቶሎ ለማባረር መታቀዱን ፍንጭ ነግር መስጫ መሆንዋ ነበረች ጽሁፉዋ።
ይሁንና ዱሮም ቢሆን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ምን ዓይነት ደባ ሲሸረብበት እንደኖረ በጥልቀት የሚያውቀው የለማ መገርሳ ቡድን ለጫጫታው ጆሮ ሳይሰጥ የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄዎች መመለስ በሚችልባቸው ስትራቴጂዎች ላይ ከህዝብ ጋር በመያየቱ ላይ ተወጠረ። ህዝቡም መፍትሄ ይሆናሉ ያላቸውን ሃሳቦች እያፈለቀ ቸግሩም የጋራ መፍትሄውንም የጋራ አደረገው፤ አመራሩና ህዝቡ እጅ ለእጅ ተያይዘው “ለኦሮሞ ህዝብ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ወደፊት” ማለቱን ቀጠሉበት። ከሁሉ በፊት በየረደጃው ያለውን አመራር ለህዝብ አቅርቦ በማስገምግም የማስቀጠልና የማስወገድ ሂደቱ የተሀድሶ የመጀመሪያ ምዕራፍ ውስጥ ትልቁን ቦታ ያዘ፤ የኦሮሞን አርሶ አደር ከቄየው ያለ ምንም ርህራሄ እያፈናቀሉ መሳውን ለኪራይ ሰብሳቢዎችና ለደላሎቻቸው ሲያከፋፍሉ የነበሩ አመራሮች በጥዋቱ መሰናበት መጀመራቸው በኪራይ ሰብሳቢው ካምፕ ግርግር ፈጠረ። የኦሮሞን አርሶ አደር የእርሻ ማሳ እንደፈንድሻ ያለማንም ከልካይ ሲያፍሱና ሲያሳፍሱ የነበሩትን ከመስመር ካስወጣ በሁዋላ የመሬት ጉዳይ በህግና በስርዓት ብቻ እንዲመራ ተደርጎ የመሬት ማናጅመንቱ ሲጠና ጉዱ እየተፈለፈለ ወጣ። በእንቨስትመንት ሽፋን የማዕድን መሬቶች በጥቂት ክራይሰብሳቢዎችና ደላሎቻቸው በየቀኑ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር ሲዛቅባቸው ሰፊው የኦሮሞ ወጣት ግን የኮቢል ንጣፍ ወረፋ መጠበቅ የ40 ቀን እድሉ እስኪመስለው ድረስ ይጠብቅ ነበር። ከአባቶቹ ያለበቂ ከሳ ወይም ያለምንም ካሳ ለአገር ልማት ተብሎ ከሚወሰድበት መሬት የሚያገኘው ጥቅም ዘበኝነት ብቻ መሆኑ የእንቨስትመንትን አሰራር ችግር መፈተሽ የግድ ነበር፤ በዚህ በኩል አብዛኛው መሬት በእንቨስትመንት ስም በህግወጥነት የተያዘ መሆኑ ሲደረስበት የአመራሩ ህዝባዊ እርምጃ እየተጠናከረ የኪራይሰብሳቢው ካምፕ መደነባበር ጀመረ።
የተሃድሶው አመራር ህዝባዊ ጉዞና የመረረውን እርምጃ ቆሞ ማየት ያልቻለው የኪራይ ሰብሳቢው ቡድን በተለይም ለአገር ኢኮኖሚ ጠንቅ የሆነው የፀረ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴም የዚሁ አብዮት አካል መደረጉ ተስፋ አስቆራጭ እየሆነ መጥቶ በለማ ቡድን ላይ የመጨረሻው እርምጃ ተወስዶ ሩጫውን ማስቆም ካልተቻለ አደገኛነቱ እየከፋ እንደሆነ የተረዳው የኪራይ ሰብሳቢ ቡድን ኦሮሚያን የማትራመስ ዘመቻውን ከኢህአዴግ ጉባኤ በፊት አጠናቆ ለስርቆቱ ሚቹ የሆኑ የዋህ የኦዴድ አባላትን በአዲስ መልክ ለማደረጀት የወጠነው እንቅስቀሴ አልሳካ ሲለው የመጨረሻ ምዕራፍ አድርጎ የወሰደው ኦሮሞን ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ለማጋጨት በምስራቅ የጀመረውን ወደ ሰሜን አዛውሮ አገሪቱን ሙሉ ለሙሉ ወደ ብጥብጥና ደም መቃባት ቀይሮ የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ በሚል ሽፋን ተሰብስቦ የቀረበውን አጀንዳ ከማፅደቅ ያለፈ ሚና እንዳይኖረው ተደርጎ የተፈጠረውን ፓርላማ “አስፈቅዶ” ኦሮሚያን በወታደራዊ አስትዳደር ስር አድርጎ የመሬት ወረራና የኮንትሮባንድ ስራውን ዳግም ለመጀመር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የደረሰ ይመስላል። 
ለዚሁ ማሳያ የሚሆኑት ደግሞ ሰሞኑን በኦሮሚያ ውስጥ በሰላማዊ ስም ሽፋን ሰልፍ እየጠሩ ሁከት በመፍጠር በብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መካከል ግጭትና ደም መቃባት እንዲፈፀም ያወጁትን ቀደም ብለው ባቀዱት መሰረት ለብጥብጥ የሚጋብዙ የሚዲያ ሽፋን በመስጠት አረመኔነታቸውን ሲገልጹ ያለምንም ሀፍረት ምንም ሰልፍ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች ሳይቀር ብጥብጥና እልቂት እንዳለ አድረገው ሲያቀርቡ በሌላ በኩል ደግሞ ክልሉ ሰላም የሌለበትና ዜጎች ያለርህራሄ እየተጨፈጨፈ ስለሆነ ማዕከላዊ መንግስት ጣልቃ መግባት አለበት እያሉ የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ እቅዳቸውን ለመተግበር ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን በአፈቀላጤዎቻቸው አማካይነት ማወጅ ጀምርዋል፤ ለዚህ ደግሞ በዛሚ ራዲዮና በENN TV የተላለፉ ዘገባዎችን ማየቱ ብቻ በቂ ነው። ብዝበዛና ጭቆና ያንገፈገፈው የኢትጵያ ህዝብ በዚህ ስውር ሴራ ይሸወዳል ብሎ መገመት አላዋቂነት ነው። ይሁንና ተስፈኞቹም አርፈው ላለመተኛታቸው ዛሬም የቀድሞውን ኦህዴድ መልሰው ለመጠፍጠፍ የጀመሩትን ስራ መቀጠላቸውን የሚሳይ የአዲሱ ኦህዴድ ከፍተኛ አመራር ተብለው የታጩትን “ህወሓት በኦሮሚያ” የሆኑ ግለሰቦችን ዝርዝር አስነብባለሁ፤ ለዛሬው ይብቃኝ።
ኦዳ ነቤ Finfinneeraa